
እናቴ በማህፀንዋ ውስጥ ከነበርኩበት ጊዜ ጀምሮ ሴት እንደነበርኩ ታውቅ እንደነበር ትናገራለች። ከእኔ በፊት ሁለት ወንድ እና ሁለት ሴት ልጆች ስለነበርዋት እንዴት የተለያዩ ፆታዎች ማህፀንዋ ውስጥ እንደሚሆኑ ታውቅ ነበር። የወንድ ልጅ ብልት ይዤ ስወለድም እጅግ ተደንቃ ነበር። እኔም ከሁለት ወይም ሦስት ዓመቴ ጀምሮ ሴት መሆኔን አውቅ ነበር። ልክ እንደ እኔ አይነት ባህሪ ካላቸው ሰዎች ጋር ብቻ ነበር መሆነ የምፈልገው። እንደ እኔ አይነት ስሜት የነበራቸው ልጆችም ሴቶች ነበሩ። ወደ ዘጠኝ አመተ ገደማም ሲሆነኝ ለወንዶች የተለየ የፍቅር ስሜትን ማሳደር ጀመርኩ። ያ ስሜት ለኔ አስደንጋጭ ነበር። ለምንድነው ምንም ለማይቀበሉኝ የጾታ ቡድኖች የተለየ የፍቅር መሳብን የማሳየው የሚለው ጥያቄ በጣም ያስጨንቀኝ ነበር።
ትራንሰ ስለ መሆን ብዙ ጊዜ ከሚያስደንቀኝ ነገሮች ውስጥ በተለያዩ የህይወት መንገዶች ውስጥ ሆኜ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የተለያዩ አይነት ግንኙነቶችን መፍጠር መቻሌ ነበር። የነበረኝንም የጾታ ሽግግር ሂደት ወደተለያዩ የምወዳቸው ሰዎች ቀስ በቀስ የማደርገው እርምጃ አድርጌ ነበር የምወስደው። ይህም ጉዞ የጾታ ሽግግሬን ከማድረጌ በፊት የጎላ ክፍተት እንዳለው መስሎ ይታየኝ ነበር። ነገር ግን የጾታ ሽግግሬን ካደረኩ በኋላ ወደምወዳቸው ሰዎች የማደርገው የጉዞ መንገዴ እየጠበበ መጥትዋል።
በአንድ ወቅት የፍቅር ጉዋደኞች የሚገኙበት መተግበሪያ/dating App ላይ የተዋወኩት ሰው ነበር። በተዋወኩት ጊዜም የጾታ ሸግግሬን ጨርሼ ትራንስ ሴት ነበርኩ። ለጾታ ሽግግር የሚጠቅሙ ሆርሞኖችን ከመውሰዴም ባሻገር ጡቶቼም በደንበ አጎጥጉጠው ነበር። ይህም ሰው ትራንስ መሆኔን ከማወቁም በላይ ለትራንስ ሴቶች ያለውን ፍቅር በተደጋጋሚ ይገልጽለኝ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤት በመጣም ጊዜ የት እና መቼ እንደሆነ ባላስታውስም የሆነ ቦታ እንደማውቀው ተሰመቶኝ ነበር። ቤቴ በመጣም ጊዜ ልዩ የሆነ የፍቅር ጊዜ ነበረን። ለሶስት ወይም አራት ጊዜም የሚያረካ ፍቅር ሰራን። በሌላ ቀን ተመልሶ ወደ ቤቴ ሲመጣ “ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እያለሁ ከሩዋንዳ የመጣ አንድ ልጅ አውቅ ነበር። በጣም ይወደኝ ነበር። ከዚህ ልጅ ጋር ያላችሁ መመሳሰል በጣም ነው የሚገርመው። እንደው ከሩዋንዳ የመጣችሁ ሰዎች ሁላ እንደዚህ ትመሳሰላላችሁ?” አለኝ። ያኔ ነበር የት እና መቼ እንደማውቀው ግልጽ ብሎ የታየኝ።
ይህ ሰውም የነገረኝም ታሪክ ስለራሴ ነበር። ዩኒቨርሲቲ በነበርኩበት ጊዜ ፍቅሬን ገልጬ ከነገርኩዋቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ ነበር። “ወንዶችን ነው የምወደው። እራሴንም እንደሴት አድርጌ ነው የምቆጥረው” ብየው ነበር። እሱም “አንተ ሴት አይደለህም፤ አንተን ሳይ ወንድ ልጅ ነው የማየው ብሎኝ ነበር”። ከአስር ዓመት በሁኋላም ሴት ሆኜ በፍቅሬ ወድቆ ማየቴ ትራንሰ ከመሆኔ ጋር ተያይዞ የመጣ ልዩ የሆነ አጋጣሚ ነበር።
የጾታ ለውጥ ላይ እያለን ሁሉም አብሮን የነበረ ሰው አብሮን ይቆያል ማለተ ይከብደኛል። ለአምስት ዓመት አብሬው የቆየሁት ከሄቲ የመጣ ሰው ነበር። አብረን ሆነን ቤት እና መኪናን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን አፍርተንም ነበር። ቤተሰቦቼንም ሳይቀር አስተዋውቄው ነበር። በጣም እወደውም ስለነበር ተጋብተን አብረን ብንኖር እጅግ ደስ ይለኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። እሱ ግን የጾታ ማንነቱን እና የፍቅር ምርጫውን ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነበር ገልጾ የተናገረው። የጾታ ለውጥ በማደርግበት ጊዜም ሂደቴን ለመቀበል እጅግ ከብዶት ነበር። የዚህም ዋነኛው ምክንያት ቤተሰቦቹ ሲያገኙኝ እሱ ያሳያቸው ከነበረው የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ማንነቱን/ hetrosexual identity እንደሚሸረሽረው ያውቅ ስለነበር ነው። ጾታው ወንድ ከሆነ ሰው ጋር አብሮ እየኖረ እንደሆነ ቢገልጽላቸውም ይህ ሰው ወደ ሴትነት እየተቀየረ ነው ብሎ ሲነግራቸው ግራ እንደሚጋቡ ይነግረኝ ነበር። ከዚህ በዘለለም ሄቲ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ምን ይሉኛል ብሎ እጅግ ይሰጋ ነበር። በነዚህ ምክንያቶችም ለአምስት ዓመታት የነበረን ጣፋጭ ጊዜያቶች ማብቃት ነበረበት።
ከሴቶች ጋር የነበርኝ ግንኙነት ከወንዶች ጋር ከነበረኝ ግንኙነቶች በተሻለ ሰላማዊ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ከሴት ልጅ ጋር ፍቅር ሲይዘኝ አስራ ሰባት ዓመቴ ነበር። በጊዜው ሩዋንዳ ውስጥ በነበረው ጦርነት ምክንያት ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ ኮንጎ መኖሪያችንን ቀይረን ነበር። በወቅቱ የወደድኩዋት ልጅም የአከራያችን ልጅ ስለነበረች በአንድ የመኖሪያ ግቢ ውስጥ ነበር የምንኖረው። ታላቅ ወንደሜም አይኑን አሳርፎባት ነበር። “ከፈለከው ሴት ጋር መሆን ትችላለህ እስዋን ግን ተዋት!” ባልኩት ጊዜ በጣም ተገርሞ ነበር። “ከዚህ ቀደም ለሴት ልጆች የፍቅር ስሜት አሳይተህ አታቅም ምን የተለየ ነገር አይተህ ነው ከዚህችኛዋ ጋር ለመጋባት የፈለከው?” የሚል ጥያቄን ሲያቀርብልኝ እኔም ላገባት ባልፈልግም ለስዋ የተለየ የፍቅር ስሜት እንዳለኝ አስረዳሁት። ጥሩ እና በጣም የቀረበ የሚባል ጓደኝነትም ነበረን። እርስ በራሳችንም የተለየ የፍቅር ሰሜት እንዳላቸው ወጣቶች እንተፋፈር ነበር።
ኮንጎን ለቀን ወደ ዛምቢያ በሄድንበት ጊዜም እኔ እና እስዋ ለረዥም አመታት ግንኙነታችንን ቀጠልን። ከዓመታት በኋላም ወደ ካናዳ መጥታ ትምህርትዋን መማር እንደምትፈልግ በገለጸችልኝ ጊዜ ከራሴ ልምድ በመነሳት የተለያዩ መንገዶችን አጋራት ነበር። በመጨረሻም ሁሉን ነገር ጨርሳ ካናዳ በመጣች ጊዜም “ወንድ ነው የምወደው!” ብዬ የፍቅር እና የወሲብ ፍላጎቴ ለወንዶች እንደሆነ ነገርኳት። እስዋም “አውቃለሁ” ስትል መለሰችልኝ። እኔም እንዴት እንዳወቀች ስጠይቃት ሌላ ለእስዋ የፍቅር ስሜት የሚያሳዩ ወንዶች ከእኔ የተለየ ጸባይን ያሳዩ እንደነበር ነገረችኝ። እውነቴን አውጥቼ በግልጽ ስለነገርኳት በመሃከላችን የተለየ የመቀራረብ ግንኙነት እንዲፈጠር በር ከፈተልን።
ለእስዋ የነበረኝ ስሜት ከአካላዊ የፍቅር ስሜት እጀጉን የዘለለ ነበር። አብረን ስንሆን ለየት ያለ የሰላም ስሜት ይሰማኛል። አንዳንዴ እንሳሳም ነበር፣ አንዳንዴ ደሞ እየተሳሳምን የተለያዩ የሰውነታችንን ክፈሎች በፍቅር እንዳስስ ነበር፣ በሌላ ጊዜ ደሞ ሳንሳሳም የተለያዩ የፍቅር ነገሮችን እናደረግ ነበር። ክንዴ ውስጥ በእቅፌ ሳደርጋት፣ ጸጉርዋ ትከሻዬ ላይ ሲሆን፣ እና እራቁት ገላችን ሲነካካ የተለየ ደስታ ይሰማኝ ነበር። እያንዳንዱ ከእርስዋ ጋር የነበረን አድራጎት ለየት ያለ ነበር። እየተገናኘን የምናደርገው ነገር ከሙሉ ፈላጎታችን የመነጨ ነበር። አንዳችን ከሌላችን የተለየ የምንጠበቀው ነገር አልነበረንም። ወደ ቤት ስተመጣ ከኔ ጋር ለመሆን ካላት ፍላጎት እንጂ ፍቅር ለመስራት ወይም የተለየ ነገር ከኔ ፈልጋ አልነበረም። ይሄ ከሌላ ወንዶች ጋር ከነበሩኝ የፍቅር ግንኙነቶች የተለየ ነበር።
ወንዶች ስለ ወሲብ ያላቸው ሃሳብ ከመርካት ጋር አብሮ የተያያዘ ነው። ወንዶች በወሲብ ጨዋታ የመጨረሻ እርካታን ካላገኙ ፍቅር እንደሰሩ አይቆጥሩትም። እስዋም የጾታ ለወጥ በማደርግበት ጊዜ ሙሉ ድጋፍዋን ትሰጠኝ ነበር። እስዋም ኩዊር ሴት እንደነበረች ትነግረኝ ነበር። በጊዜው የወንድ ሰውነት ቢኖረኝም እናደርገው የነበረው የወሲብ ጨዋታ ከሌላ ሴት ጋር ሆኖ እንደሚሰማት ትነግረኝ ነበር።
የጾታ ለውጥ ሂደት ላይ ሆኜ እየተለዋወጠ የነበረውን ሰውነቴን ከተለያዩ ሰዎች ጋር በመገናኘት እና የተለያዩ አይነት የወሲብ ጨዋታዎችን በማድረግ እራሴን ለመቀበል እጅጉን እረድቶኛል። እያንዳንዱ የነበረኝን የሰውነት ለውጥ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ለሚፈጠር ቅርበቶች የተለያዩ በሮችን ይከፍቱልኝ ነበር። የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ አይነት የጾታ ማንነት እና ባህሪ ያላቸውን ሰዎች ይመርጣሉ። አንዳንደ ሰዎች እንስታዊ ጸባይ ያላቸውን/faminine ወንዶች ሲወዱ፣ አንዳንድ ሰዎች ደሞ በተለምዶ የተቃራኒ ጾታ አለባበስን የሚያዘወትሩ ሰዎችን ይወዳሉ፣ አንዳንድ ሰዎች ደሞ በጾታ ለወጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎችን ማለትም ለሂደቱ የተለያዩ ሆርሞኖችን ወስደው ጡት ያላቸውን ሰዎች ይመርጣሉ።
በተለያዩ የጾታ ለወጥ ሂደቶች ውስጥ ሆነን በያአንዳንዱ በምናደርገው የለወጥ ደረጃዎች ውስጥ ያለንን ማንነታችንን የሚወዱልን ሰዎች እናገኞለን። ችግሩ ሰዎች ባገኙን የለውጥ ሂደት ውስጥ ብቻ እንድንቆይ መፈለጋቸው ነው። በተለያዩ የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆናችንን አይረዱትም። በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ውሰጥ እራሳችንን ስናገኝ ደፍረን “የጉዞዬ መጨረሻ ላይ አልደረስኩም!” ማለት ያስፈልጋል። በተለያዩ የጾታ ለወጥ ሂደት ውሰጥ ሆኜ ለፍቅር ጨዋታ ክፍት መሆኔ የተለያዩ ሰዎችን በደንብ እንዳውቅ እና እንድረዳ እረድቶኛል።
ሰውነቴ ሙሉ ለሙሉ ወደሴትነት የመለወጥ ሂደቱን ከጨረሰ በኋላ ዓለምን ለመዞር ወሰንኩ። ይህም በዓለም ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሰዎችን እና ባህላቸውን ለማወቅ ካለኝ የተለየ ጉጉት የተነሳ ነበር። ይሄንንም ለማሳካት በወሲብ ንግድ ስራ ላይ እራሴን አሰማራሁ። በወሲብ ስራ ውሰጥ ሆኜ የተለያዩ የዓለም ክፈሎችን ከማየቴም በላይ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የተለየ የፍቅር ግንኙነትን ለመፍጠር እረድቶኝ ነበር። ከዚህም ባሻገር በወሲብ ስራ ወደ አፍሪካ ለመመለስ እና ከአፍሪካዊያን እህቶቼ እና ወንድሞቼ ጋር እጓጓለት የነበረውን ፍቅር ለማጣጣም ችዬበታለሁ። የወሲብ ስራ እውነተኛ ማንነቴን በጥልቀት እንድረዳም አድርጎኛል። በወሲብ ስራ ውሰጥ ሆኜ ከተዋወኩዋቸው ሰዎች ውስጥም እስከ አሁንም ጉዋደኞቼ እና አፍቃሪዎቼ ሆነው የቀጠሉ አሉ። ከእነዚህ ሰዎች ውሰጥ አብዛኛዎቹ እራሳቸውን እንደተቃራኒ ጾታ አፍቃሪዎች አድርገው ነው የሚገልጹት። አንዳንዶቹ ባለትዳር ሲሆኑ እኔም ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ አፍቃሪያቸው ነኝ። አንዳንዶቹ ደሞ የፍቅር ጓደኞች የሌሏቸው ወንዶች ነበሩ።
የጾታ ለውጥ ሂደቴን ከመጨረሴም በፊት የወንድ የብልት አካል ስለነበረኝ ብዙ ጥያቄ ያቀርቡልኝ ነበር። በዚህ ምክንያት አንዳንድ አገኛቸው የነበሩ ሰዎች ምቾት አይሰማቸውም ነበር። ይሄም ሂደት እራሴን፣ ሰውነቴን፣ ብሎም ጸባዬን እንድወድ አድርጎኛል። እነዚህ ሰዎችም ከእኔ ጋር ፍቅር መስራትን እየወደዱ ሲመጡ፣ እኔም ከትራንስ ሴት ጋር ሆነው ባለማወቃቸው ብቻ ከእኔ እንዲርቁ ከማድረግ ይልቅ የህይወት መንገዳቸውን መረዳትን እየተማርኩ መጣሁ።
አሁን ሙሉ ለሙሉ የትራንስ ሴት ከሆንኩ በኋላ ከሴቶች ጋር ያለኝ የወሲብ ልምድም እጅግ ተቀይርዋል። የወንዶች የአካል ክፍል እያለኝ ሴቶች በቂ በሆነ ሁኔታ እንደሴት እንደማያዩኝ ተረድቼለሁ። የወንድ አካል በመያዜ ብቻ ተያይዘው የሚመጡ በፓትሪያርኪይዊ ስረአት ውስጥ የሚገኝ አድሏዊነት እንዳለም ተረድቻለሁ። አሁን ግን በሴቶች የተለየ ተቀባይነት እንዳለኝ ይሰማኛል። በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች ሴቶች ጋር ያለኝ የእህታዊነት ስሜት ብዙም ሳልሞክር በቀላሉ ይመጣል። አሁን ላይ በወንዶች እይታ ውስጥ ሆነን ተመሳሳይ የሴትነት ልምድ ስላለን እና አንድ ሴት ከሌላ ሴት የበለጠች ሆና ባለመታየትዋ ልዩ የሆነ ግንኙነተን ይፈጥርልናል።
አፍቃሪዎቼ የተለያዩ የፍቅር ጉዋደኞች እንዳሉኝ ከማወቃቸውም በላይ የተለየ ያለመመቸት ስሜት አያሳዩኝም። ይህም ከአንድ ፍቅረኛ ጋር ብቻ የተገደበ ግንኙነት ውስጥ ስላልሆንኩ ነው። ለፍቅር እና ወሲብ የመሳቤ ፍላጎቱም የመነጨው በሙሉ ነጻነት ላይ መሆኑን ጠንቅቀው ይረዳሉ። ስለወሲብ ህይወቴ ሳስብ እጅግ የጎለበተ እና ፍጹም የእርካታ ሰሜት ይሰማኛል። ለወሲብ ያሉኝን የተለያዩ ፍላጎቶች እና ስሜቶች ከተለያዩ ሰዎች ጋር በመሆን እርካታን አገኝበታለሁ። በፈረንሳይኛ ማበብ ብለን እንገልጸዋለን። “እኔ የተሟላ እና ያበበ የፍቅር ህይወት አለኝ!”
ሶላንጅ
ተፈፀመ።