Categories
Uncategorized

ሶላንጅ

ሶላንጅ የአርባ ስድስት አመት ኩዊር ሴት ነች። እራስዋን ለመግለጸ ኩዊር የሚለውን ቃል ትመርጣለች፣ ምክንያቱዋም ይህ ቃል ሰፊ እና ሁሉን አቃፊ ስለሆነና ለተቃራኒ ጾታም መሳብዋን እና የሄትሮሴክሽዋል  ማንነትዋን ጠቅልሎ ስለሚገልጽ እንደሆነ ትናገራለች። ሶላንጅ ትውልድዋ ከሩዋንዳ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በአቡጃ ውሰጥ ስትኖር ካናዳንም እንደ ሌላኛው ቤትዋ ትቆጥረዋለች።

አንድ ቀን እየጸለይኩ የሆነ ድምጽ ከውስጤ ሰማሁ። “ እግዚያብሔር ነው እንዲህ አድርጎ የፈጠረሽ። እግዚያብሔር ስህተት አይሰራም። እግዚያብሔር እንደዚህ አድርጎ በተለየ ሁኔታ የፈጠረሽ ልዩ የሆነ አላማ ስላለው ነው።” የሚል ነበር። 

ወዲያው ህይወቴን እንደራሴ አድርጌ መኖር እንዳለብኝ እና ትልቁ ሃጥያት እራሴን በእውነተኛው ማንነቴ አለመኖሬ መሆኑን ተረዳሁ። ይህንን እውነት ለመረዳት ሃያ አምስት ረዣዥም ዓመታቶች ከመውሰዱም ባሻገር ከሩዋንዳና ከቤተሰቦቼ ርቄ መኖረ ነበረብኝ። ሼርብሩክ፣ ካናዳ ውስጥ ሰዎች ምን መስራት እና ምን መልበሰ እንዳለብሽ አይነግሩሸም። እራቁትሸን መንገድ ላይ ብትሄጂ እንኳን ፖሊሶች እርቃነ ስጋሸን እንድትሸፍኚ ብቻ ነው የሚያረጉሽ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወቴ በራሴን ከመሆኔም በላይ ለራሴ ህይወት የሚያስፈልገኝን ማወቅ ብሎም መወሰን ነበረበኝ። ሁልጊዜ ቤተሰቦቼን ለማስደሰት የምሮጥ ህጻን ልጅ እንዳልሆንኩ እና ህይወቴን ለራሴ መኖር እንዳለብኝ ተረዳሁ። አንድ ቀን ወደ አንድ የስልክ የእርዳታ ጥሪ በመደወል እኔን የሚመስሉ ሰዎች (ኩዊር ሰዎች) ይገኙበታል ስለተባለ አንድ መጠጥ ቤት ሰማሁ። እኔን የሚመስሉ ሰዎች  ጋር ለመገናኘት ብዙ ጊዜ ከመጠበቄ የተነሳ አንድ ምሽት በሚገርም ተነሳሽነት እና ወኔ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሰማሁት ኩዊር ቦታ አመራሁ። መጠጥ ቤቱ በነጮች የተሞላ ቢሆንም፣ ሁለት ጥቁር ሰዎች በማየቴ ተረጋጋሁ። 

ሼርብሩክ እጅግ በበዛ መልኩ የነጮች ከተማ ከመሆንዋ የተነሳ፣ እኔን የሚመስሉ ሰዎች በአካባቢዬ መኖራቸው በህጻንነቴ በተደጋጋሚ እሰማው ወደ ነበረ ታዋቂ የፈረንሳይኛ ዘፈን ወሰደኝ። ዘፈኑም ስለሁለት ትምህርት ቤት ውስጥ ስለነበሩ ልጆች እና እርስበርሳቸው  ስለነበራቸው ፍቅር የሚያወጋ ነበር። ቃላቶቹም “…….የተለመደ በሽታ ነው? ወንዶች ሌላ ወንዶቸን መውደዳቸው?…” የሚል እንደምታን የያዘ ነበር። ይህን ዘፈን እየሰማሁ “የሚዘፍኑት ወንዶች  ስለወንዶች ስላላቸው ፍቅር ነው? እንዴት ሊሆነ ቻለ?” ብዬ እናቴን ጠይቄያት ነበር።

እስዋም “እኛ አፍሪካዊያን  ውሰጥ  እንደዚህ አይነት ነገረ የለንም። በጥቁሮች ህብረተሰብ ውስጥ እንደዚህ አይነቱ ነገር አይፈጠርም። አንደዚህ አይነት ስሜቶች የነጮች ማህበረተሰብ ውስጥ ብቻ የሚፈጠር ሲሆን ይህም የሆነው ነጫች ሃብታሞች ስለሆኑ የተለያዩ ነገሮችን መሞከር ስለሚፈልጉ እና ይህንንም ለማሳካት  መንገድ ስላላቸው ነው። እነዚህ ፍላጎቶች ላንተ እንደ አንድ አስፈላጊ ነገር ሊሆኑ አይችሉም። ምክንያቱም አንተ ለህይወትህ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለምሳሌ እንደ ምግብ አይነቱን ለማሙዋላት ቀና ደፋ ስለምትል ነው። ለዚህም ነው እነሱ ሌላ አይነት ፍቅር እና ወሲባዊነትን የሚፈለጉት።” ስትል እንደነገረችኝ አስታውሳለሁ። “ወንድ ልጄ ነው ብለሽ የምታስቢው ልጅሽም ተመሳሳይ ስሜት አለው!” ልላት ብፈልግም በመስማማት ጭንቅላቴን በማወዛወዝ አለፍኩት። በእርግጥም ሌሎች ሰዎች እኔ ያለኝን ሰሜት እንዳላቸው ማወቄ በትንሹም ቢሆን ጠቅሞኝ ነበር። 

ምንም እንኳን ሰዎችን ለመተዋወቅ እና ለማግኘት ቢሆንም ወደ ኩዊር መጠጥ ቤት የሄድኩት እንደገባሁ ያየሁዋቸውን ሁለት ጥቁር ሰዎች ለማነጋገር በጭራሸ አልሞከርኩም። ይልቁንም ቲም እራሱን ለማስተዋወቅ ተጠጋኝ። ልክ እንዳየሁት ወደድኩት። ቲም ወንድ ሆኖ ለወንዶች የፍቅር ስሜት ያለው ሲሆን እኔንም እንደሌላ ወንድ በመቁጠር ከኔ ጋር ሊያድር እንደሚፈልግ ነገረኝ።

በጊዜው ሃያ አምስት አመቴ ሲሆን እስከዚያ ድረስም ከሌላ ሰው ጋር ምንም አይነት የወሲብ ልምድ አልነበረኝም።  ምንም እንኩዋን ሰውነቴ ቲምን ቢፈልገውም ውስጤ ግን ፈርቶ ነበር። “ነገ በሰፊው የፍቅር ጊዜ እናሳልፋለን። “ዛሬ ዝግጁ አይደለሁም” እያልኩ የተለያዩ ምከንያቶችን እሰጠው ጀመር። በውስጤ ግን ቲምን አልጋዬ ውስጥ በማድረግ ማለሜን ቀጠልኩ። እራቁቴን ከሱ ጋር ስሆን፣ ሰውነቴ እሱ ውስጥ ሲሆን፣ ወይም እሱ እኔ ውስጥ ሲሆን፣ አንድ ሆነን ስለ ሌላችን የሚሰማንን ፍቅር ስንገልጽ እና አብረን ስንሆን እያሰብኩ በደስታ እማልል ነበር። 

አንድ ቀን ዝግጁ ነኝ ብዬ በመወሰን ቲምን ወደ ቤቴ እንዲመጣ ጋበዝኩት። ምንም እንኩዋን የስቱዲዮ አፓርትመንቴ ሰፋ ያለ ቦታ ቢኖረወም፣ ከሁሉም አቅጣጫ አልጋዬን ማየት ይቻል ነበር። በምወዳቸው ቀለማት ቀይ እና አረንጓዴ የሆኑ ሻማዎችን አበራሁ። ከሻማዎቹ የሚወጣው የቫኒላ መአዛም ቤቴን አውዶት ነበር። የተለያዩ አበቦችም በመግዛት በተለያዩ ቦታዎች ላይ በማድረግ አስጌጥኩበት። አሳ፣ ድንች እና አስፓራጉስ ለዚህ ልዩ ምሽት ይሆናል  በማለት አዘጋጀሁ። ምርጥ የሆነ ወይንም ከፈትኩ። ቲም ቤቴ ከምሽቱ አስራሁለት ሰዓት ተኩል ቢደርስም እስከ ለሊቱ ስምንት ሰአት ድረስ አብረን አመሸን። የመጀመሪያውን አራት ሰዓታት ስንበላ፣ ስንጠጣ እና ስናወራ አሳለፈን። በስተመጨረሻም ከምሽቱ አራት ሰአት ሲሆን ወደ አልጋዬ ሄድን። 

እንደዚህም አለኝ

ቀስብለህበራስህጊዜእንድትደሰትነውየምፈልገው።እስከፈለከውድረስመሄድትችላለህግንገደቦችህንአክብር።ምንምነገርካመመህንገረኝ።እራስህንእናገደቦችህንአልፈህእንድታስደስተኝአልፈልግም።ስለራስህደስታአስብ።አንተእንደምትፈልገውምራኝ።እኔየምፈልገውንአውቃለሁነገረግንአንተየምትፈልገውንእንድታረገነውየምፈልገው።ሰውነትህንበደንብአውቀህምንእንደሚያረካህእንድትረዳእፈልጋለሁ።እኔበወሲብየሚገኘውንደስታበደንበአውቃለሁ፣አንተምይህንንደስታእንደታገኝእኔንተጠቀምብኝ።አብረንደሰየሚልህንሁሉማድረግእንችላለን፣በፈለከውሰዓትምማቆምእንችላለን።” 

ከኔ ጋር በልቤ ውስጥ ተቀርጸው ስለቀሩት የቲም ዉብ እና ጠንካራ ቃላቶች ሁሌም አመሰግነዋለሁ። ስለስሜቴ፣ ስለ ወሲባዊ ምርጫዬ እና ስለገደቦቼ እንድረዳ እጅግ ጠቅመውኛል። አዲስ ፍቅረኛም ስተዋወቅ “እሱ አያስደስተኝም”፣ “በቃኝ”፣ “ምቾት እየተሰማኝ አይደለም” ማለትን ችያለሁ። 

ቲም ሰውነቴን እንዴት አንድ ሺ ጊዜ ስለመሳምም አስተምሮኛል። ሁሉም የሰውነት ክፈሎቼን ለወሲብ እርካታ መጠቀሚያ ሊሆን እንደሚችል አሳይቶኛል። ቲም ውብ የነበረውን የመጀመሪያውን ምሽታችንን “የአንድ ሺ የመሳሳም ምሽት” ብሎት ነበር።

ሙሉ ሰውነቴን ከጭንቅላቴ አንስቶ እስከ እግሬ ጣቶች በመሳም የተለየ ደስታን ሰጥቶኛል። ምንም የሰውነቴ ክፍል ሳይዳሰስ የቀረ አልነበረም። የመጀመሪያ የወሲብ አጋጣሚዬ ከሱ ጋር ስለነበረ እራሴን እንደልዩ እድለኛ አድርጌ እቆጥራለሁ። ለረጀም ጊዜ ስለራሴ አካል እና ምን አይነት ሰው ስለመውደዴ የነበረኝን ከባድ ህፍረት በተወሰነ መልኩ አስወጥቶልኛል። ቲም በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ያፈቀርኩት ሰው አልነበረም፣ ነገረ ግን ፍቅሬን እንደ ልቤ ልገልጽለት የቻልኩት የመጀምሪያው ሰው ነበር። 

ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር የያዘኝ የአስራ አራት ዓመት  ልጅ እያለሁ በጣም እቀርበው ከነበር እና ከልጅነታችን ጀምሮ አብሬው ከተማርኩት ልጅ ጋር ነበር። እድሜያችን ወደ አስራ አራት ዓመት ገደማ ነበር። የምንማረውም አንድ ትምህርት ቤት ከመሆኑመ ባሻገር አንደ ክፍል ውስጥ ነበርን። ሁለታችንም እግዚያብሔርን በጽኑ እንወድ ነበር። የሚኖርበት ቤት ከትምህርት ቤታችን እና ሁለታችንም እንሄድበት ከነበረወ የካቶሊኮች ቤተክርስቲያን አማካኝ ላይ ስለነበረ፣ አዘውትሬ ቤቱ በመሄድ አብረን ወደ ቤተክርስቲያን እንሔድ  ነበር። ቤተክርስቲያን ለመሄድ ዋነኛው መነሳሺያዬም እሱ ነበር። በጊዜው አድጌ ቄስ የመሆን እቅድ ነበረኝ። ምክንያቱም ወደ ገነት መሄድ እፈልግ ስለነበር።

ወሲብ ለማረግ ብቸኛው ምርጫዬ አድጌ ሴት ማግባት እንደነበር ማሰቡ ብቻ እጅግ በጣም ይከብደኝ ነበር። ቄስ ከሆንኩ ግን ጥሩ ሰው ሆኜ ለወሲብ ያለኝንም ፋላጎት ሊያጠፋልኝ እንደሚችል አምን ነበር። ጥሩ ክርስቲያን በመሆነ የስጋ ፍላጎቴን መቆጣጠር እንደምችል አስብ ነበረ። እንደ ሌላ ሰዎች መሆን አልፈልግም ነበር። የሰይጣን አምላኪ መሆን አልፈልግም። አንድ ቀን ወንድሜ እራሴን ስለማርካት (ማስተርቤሽን) ነገረኝ። የምትፈልጋትን ሴት እያሰብክ እራሴን በመንካት መርካት እንደምችል። ስለምወደው  ጓደኛዬ በዛ መልኩ ማሰበ ከመጀመሬ በፊት፣ ወንድሜ የነገረኝ ነገር ለሰሚው ግራ የሚገባ ሆኖብኝ ነበር።

እራቁቱን ሆኖ፣ ጸጉሩን ስዳስስ፣ እና በእቅፉ ውሰጥ ስሆን ማለመ ጀመርኩ። ከዛም አልፎ ወደታችኛው ሰውነቱ ሃሳቤን በመላክ ህፍረተ ስጋው ምን እንደሚመሰል በሃሳበ እስል ጀመር። ህልሜ ግን የኔ እና የኔ ብቻ ነበር። ምክንያቱም ይህንን ከተፈጥሮ ውጪ ነው ብዬ ያሰብኩትን ስሜት እንዴት ለሌላ ስው አጋራለሁ? ከአስር  ዓመት በኋላ ሰውነቴ ወደ ሴት የመለወጥ ሂደቱን ሲጀምር፣ ጎደኛዬ የመጀመሪያው የነገርኩት ሰው ነበር። እሱም ሴት ሆኜ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚነካኝ ሰው እንደሚቀና ነግሮኝ ነበር። በአሁን ሰዓት እሱ ቄስ ሲሆን ለእግዚአብሔር ላለው  የጎለበት ፊቅር ሁሌም እንደሚያመሰግነኝ ይነግረኛል። 

በነዛ ጊዜዎች ሼርብሩክ ውስጥ ከአፍሪካ የመጡ ሰዎችን ማግኘት ቀርቶ ባጠቃላይ ጥቁር የሆኑ ሰዎችን ማግኘት እምብዛም አልነበረም። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ እራሴን እንደምንም በማነሳሳት ኲዊር ቦታዎች ላይ አያቸው የነበሩትን ሁለት ጥቁር ሰዎች ደፍሬ አነጋገርኩዋቸው። ነገር ግን ሁለቱም በነጭ ቤተሰቦች ጉዲፈቻ የተሰጡ ከመሆኑም በላይ ስለ ጥቁር ባህል እምብዛም አያውቁም ነበር። አንድ ቀን ሼርብሩክ ውሰጥ አውቶብስ ይዤ ስሄድ በጣም የሚያምር አፍሪካዊ ሰው አየሁ። መላክ መስሎ ነበር የታየኝ። እድሜውም ወጣት በሃያዎቹ አጋማሽ ላይ ያለ ይመስል ነበር። የቆዳው ቀለም ፣ አይኑ፣ አፍንጫው፣ ሁሉ ነገሩ ትንፋሼን አጠፋው። እሱን በማየት ብቻ እራሴን ሰቼ የምወድቅ መሰለኝ። ከየት ድፍረቱን እንዳመጣሁት ባላቅም ቀርቤ እራሴን አስተዋወኩ። እሱም ሌላ አፍሪካዊ በመተዋወቁ ደስ ብሎት ነበር።

ቴሪ አመጣጡ ከቤኒን ሲሆን ሼርብሩክ ውስጥ ትምህርት ከጀመረ ሶስት ወር አልፎት ነበር። በሶስት ወር ቆይታውም እኔ የመጀመሪያው ያገኘኝ አፍሪካዊ ነበርኩ። ወዲያውም ጥሩ ጎደኛሞች ከመሆናችንም አልፎ እኔ በፍቅሩ ወደኩ። የተለያዩ የአፍሪካ ምግቦችን ለማብሰል እና ስለ ጥቁር ማንነት እና የተለያዩ ልምዳቻችን ለማውራት አዘወትረን እንገናኝ ጀመር። ሁሌም አብሬው በማሳልፈው ጊዜ እጅግ ደስተኛ ነበርኩ። ከሱ ጋረ በመሆኔ ብቻ እደሰት ነበር።

ከጥቂት ወራቶች በኋላ ትምህርቴን ለመቀጠል ወደ ሞንትሪያል በሄድኩበት ጊዜ አንድ ቀን ቴሪ ሊጠይቀኝ መጣ። አብረን ስናድር የመጀመሪያ ቀናችን ነበር። አልጋዬ ለአንደ ተማሪ የተሰራች ስለነበረች፣ በከፊል እርቃኑን የነበረውን ቴሪን ለመጨመር እጅግ ጠባብ ነበረች። በዚህም ሁኔታ ውስጥ ሆነን ለሱ ያለኝን ሰሜት ከመናገር ልቆጠብ አልቻልኩም። ያቺ ምሽትም በሃይለኛ ስሜት በተሞላ ፍቅር አለፈች። በማግስቱም ቴሪ ተነስቶ ሄደ፣ ያቺ ምሽትም ቴሪን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁበት የመጨረሻ ቀን ነበር።

በተደጋጋሚ ለምልክለት የስልክ መልእክቶች እና ጥሪዎችም ምንም ምላሽ ላገኝ አልቻልኩም። ምንም እንኩዋን በዛች ልዩ ምሽት ያደረግነው ነገር ሁላ በሙሉ ፈቃደኝነት የተሞላ ቢሆንም፣ ተስፋ ከመቁረጤ የተነሳ ይቅርታን የሚጠይቅ መልእክት ላኩለት። ያ አጋጣሚ በፍቅር ለመጀምሪያ ጊዜ ልቤ የተሰበረበት ወቅት ነበር። አብረን ያሳለፍናቸው ምርጥ ጊዜዎች በዚያች የአንድ የስሜት ምሽት ሊጠፋ ይችላል የሚለውን መቀበል እጅግ ከብዶኝ ነበር። ቴሪን ሁሉንም ነገሩን ነበር የምወድለት። ስለ እግር ኳስ ወይም ትምህርት ቤታቸው ውስጥ ስለሚደረግ ውድድር እና እንዴት እንደሚያሸንፍ በስሜት ሲያወራልኝ መስማት በጣም ያስደሰተኝ ነበር። ዝም ብሎ አብሮኝ ሲሆን እንኩዋን በጣም እወደው ነበር። 

አሁን ላይ ሆኜ ስለዛች ምሽት ሳስብ ቴሪ ዝግጁ እንዳልነበር እረዳለሁ። ያደረግነውን ነገ ስናደርግ ምንም አይነት ስም አልሰጠነውም ነበር። እናም ምሽቱንም ስንጨርስ እራሳችንን ማን እንደነበርን በደንብ እናውቅ ነበር። ቴሪ ወንድ ሆኖ ሴቶችን የሚያፈቅር እንደመሆኑ ሳያውቀውም ቢሆን ውስጤ ካለችው ሴት ጋር የተለየ ግንኙነት ፈጥሮ ነበር። ነገር ግን እንደ እኔ በወንድ ሰውነት ውስጥ ሴት ይኖራል የሚለውን በጭራሽ አያውቅም ነበር። እኔን እንደሴት ስላላየኝም ውስጡ ስለእኔ በተፈጠረው ስሜት እጅግ እንደተረበሸ እረዳለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *