ባልድዊን “The Fire Next Time” ሲተረጎም የቀጣዩ ጊዜ እሳት በተሰኘው ጽሁፉ ሦስት ቁልፍ የሆኑ የፍቅር መንገዶችን በመለየት እንዴት አሜሪካ ወሳኝ በሆነው ታሪካዊ ጊዜ ላይ እነዚህ መንገዶች እንደ አዲስ ሊገነብዋት እንደሚችሉ ያሳየናል። በመጀመሪያ ባልድዊን የጥቁሮችን ፍቅር እንደ ዋነኛ የነጮች ከሃጢያት መጽጃ መንገድ አድርጎ ያቀርበዋል። አሰራ አራት አመት ስለነበረው የእህቱ ልጅ ብሎም በማያያዝ ስለጥቁር ሰዎች በማስመልከት እንዲህ ብሎ ጽፍዋል።
“እባክህ ግልጽ ለመሆን ሞክር፣ ውድ ጄምስ፣ ስለወጣትነትህ በጭንቅላትህ ላይ ከሚንበለበለው መዐበል ውሰጥ፣ በነጮች ተቀባይነትን ማግኘት ብሎም መቀላቀልን ከማግኘት በዘለለ የሚገኘው እውነት ላየ ይሁን። የእነሱም አንተን መቀበል አለባቸው የሚለው ቦታ የለሽ ግምታቸው ምንም ተጨባጭነት የለውም። ውዱ ጎደኛዬ አስፈሪው ነገር ግን አንተ እነሱን መቀበል ግዴታህ ነው ስልህ በአጽዓኖ ነው። መቀበል ግድ ይልሀል እናም ስትቀበላቸወ በፈቅር መሆን አለበት ምክንያቱም እነዚህ ንጹህ ሰዎች ምንም ሌላ ተስፋ የላችውምእና።”
ባልድዊን እ.ኤ.እ በ1963 በሰፊወ በነጭች ሰዎች፣ ብሎም በተለያዩ ተቐማቶች፣ እና መለኪያዎች ጥቁሮችን መቀበል ወይም መቀላቀል በሚሉ አስተሳሰቦች እና ግምቶችን በእጅጉ ያወግዝ ነበር። የልቁንም እነዚህን አስተሳሰቦች በመገልበጥ እንደውም ነጮችን፣ የተለያዩ የአሜሪካ ተቐዋማቶችን፣ እና ደንቦችን ጥቁር አሜሪካዊያኖች በራሳቸው ጊዜ በመቀበል አሜሪካን ሊከይሩ እንደሚችሉ አጥብቆ ይገልጻል። ባልድዊን በዘር ላይ በተመሰረተ ህጋዊ መለያየት ከማብቃቱ ሁለት አመት ቀደም ብሎ፣ ጥቁሮች ነጮችን እንዲቀበሉ ብቻ ሳይሆነ በፍቅር እንዲቀበሉ ወትውትዋል። የጥቁር ሰዎችን ፍቅር እንደዋና መሳሪያ አድርጎ በመመደብ እና የነጮችን ነፃነት በብሄራዊ ደረጃ ሊያመጣ እንደሚችል አጥብቆ ጠይቌል።
ሁለተኛ፣ ባልድዊን የአሜሪካን የዘር ችግር የነጮችን የፍቅር የለሽነት ምልክት አድርጎ ያሳየናል። እንዲህም ብሎ ጽፍዋል፤
“በዚህ ሃገር የሚገኙ ነጮች እርሰ በራሳቸው የመቀበልን እና የመዋደድን ልምድ መማር አለባቸው። ይህንንም ማድረግ ሲችሉ ፣ ነገ አይሆንም ወይም መቼም አይሆንም፣ የጥቁር ሰዎች ችግር አይኖርም ምክንያቱም ከዛ ጊዜ በህዋላ አስፈላጊ አይሆንም።”
ይህ ጠንከር ያሉ ሃስቦችን የያዘ ጽሁፍ፣ ባልድዊን እንዴት የፊቅርን ግላዊም ሆነ ፖለቲካዊ ጥቅም አስረግጦ እንደሚገልጽ ከማሳየቱም ባሻገር፣ የነጮች እራሳቸውን መቀበል በአሜሪካ ላለው በዘር ላይ የተመሰረተ ችግር መቅረፊያ አድርጎ ይጠቀምበታል። እንደ ባልድዊን አገላለጽ የነጮች ማንነት የተመሰረተው በነዚህ የራሰን መቀበል እና የማረጋገጥ ህጎች እንጂ፣ የሀይል የበላይነት ወይም የንጹህነት ማንነተን እንደማይጠየቅ ብሎም የራስን ማንነት እንደማይለካ ያሳያለ።
በሦስተኛም ባልድዊን በነጭ እና በጥቁር ዘሮች መካከል የሚፈጠርን ፍቅር እንደ አንድ ልዩ የሆነ ሀገራዊ ሃሳበ አቅርቦታል። ይህ አረፍተነገርም ከThe Fire Next Time/የቀጣዩ ጊዜ እሳት ላይ በተደጋጋሚ የሚጠቀሰ መስመር ነው።
“እኛ ማለትም በአንጻራዊ ንቁ የሆንን ነጮች እና በንጻራዊ ንቁ የሆንን ጥቁሮች፣ ልክ እንደ ፍቅረኛሞች በመሆን አጥብቀን በመሻት የሌሎችን ንቃተ ህሊና መፍጠር አለብን። ስራችንንን የሚያደናቅፍ ከሌለ፣ ትንሽ ብንሆንም የዘር ቅዠታችንን አቁመን የሃገራችንን ስኬት ማምጣት ብሎም የአለመን ታሪክ መቀየር እንችላለን።”
በ1963 የተሳሳተ አመለካከትን ለማጥፋት እና ህጋዊ የዘር መቀላቀልን ለማምጣት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በነገሱበት ወቅት፣ እንደ አዲስ ሃሳበ ሆኖ በተለያዩ ዘሮች መካከል የሚፈጠር የፍቅር ታሪክ በርግጥም ስሜትን የሚያነሳሳ እና የሚቀስቅስ ነበር። በሃገራዊ ደረጃ ለውጥ ለማምጣት ምን ያህል አደጋ፣ ጥረተ እና የመቀራረብ ስሜት እንደሚያስፈልገ ብሎም ምሳሌ የሚሆን የጋራ ራስን የመለወጥ ሂደትን በማቅረብ እንዴት ከባደ የሆነው ስኬት እንደሚመጣ አሳይትውል። የባልድዊንን የተለያዩ የፍቅር ታሪኮችን በመጠቀም የሚጽፋቸው ጽሁፎች በጸሃፊው በተለያዩ የሲቪል መብት እንቅስቃሴዎች በሰፊው ነግሰውበት በነበሩት አመታቶች ላይም ይታያሉ።
ጸሃፊው የነጭ ንጹህነት እና ፍቅር አልባነትን እንደዋነኛ ጨብጥ አድርጎ በ1956 Giovanni’s Room/ የጆቫኒ ክፍል ተብሎ በወጣው ጽሁፉ ላይ አብራርቶታል። በተለያዩ ዘሮች መካከል ስላለ የፍቅር ታሪክ እና ተያይዞ ሰለሚመጡ አስቸጋሪ ውጣውረዶች ደግሞ፣ Another Country/ሌላኛው ሃገር በሚለወ ሦስተኛው መጽሃፉ ላይ አትቶታል። ባልድዊን If Beale Street Could Talk/የቢል ስትሪት ማውራት ቢችል ኖሮ የሚለውን ልብወለዱን ከጻፈ በሁላ ያሉት ጽሁፎቹ ላይ ብዙ ለውጦችን አይተናል። በዚህ ጽሁፉም ባልድዊን በጥቁር ሰዎች መካከል ስላለ ፊቅር ቀስቃሽ እና አነሳሽነት አሳየተዋል። If Beale Street Could Talk/የቢል ስትሪት ማውራት ቢችል በጥቁር የፍቅር ታሪክ ላይ ብቻ የሚያተኩር የመጀመሪያው የባልድዊን ልብወለድ ነው። ብሎም ደራሲው ከጻፋቸው ጽሁፎች ውስጥ በሴት ተራኪ የተተረከ ብቸኛው ጽሁፍ ነው። ይህ ጽሁፍ የሚያጠነጥነው 21 አመትዋ ቲሽ እና በ22 አመቱ ፍቅረኛዋ ፎኒ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ነው። በመጸሃፉ መግብያ ላይ ቲሽ ፍቅረኛዋ ፎኒ በሃሰት የአስገድዶ መድፈር ክስ ወደ እስር ቤት ከተላከ ብዙም ሳይቆይ እርጉዝ መሆንዋን ታውቃለች። በቲሽ ተራኪነት ታሪኩ እርግዝናዋን እና እጅግ አድካሚ ስለነበርው ፎኒን ለማስፈታተ የተደረገ ጥረት እያስቃኘ ይሄዳል። እናም ተከታታይ በሆኑ የድሮ ብልጭታዎች፣ ሁለቱ የፈቅር ወፎች እና ቤተሰቦቻቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ እንዴት እንደተጣመሩ ይተርካል።
If Beale Street Could Talk/የቢል ስትሪት ማውራት ቢችል ጥብቅ በሆን መልኩ ስለ አሜሪካ አፋኝነት ቢተርክም፣ ስልታዊ የሆን ዘረኝነትን የሚያሳየው የታሪኩ ሂደት ስለሁለቱ ጥቁር ወጣት ጥንዶች እና ቤተሰቦቻቸው የሚያውጠነጥነውን ታሪክ ባልሸፈነ መልኩ ነው። ወደ ጥቁር ፊቅር ለተደረገው መሸጋገር ዋነኛው ምክንያት፣ If Beale Street Could Talk/የቢል ስትሪት ማውራት ቢችል በጥቁር የስነጥበበ ንቅናቄ ጭራ ላይ መታተሙ ነበር። የጥቁር የባህል ተቐማትን በመፍጠር፣ ይሀውም መጽሄቶች፣ ጆርናሎች እና የጥቁሮችን ንቃተ ህሊና ለማሳደግ ቁርጠኛ የሆኑ ማተሚያ ቤቶችን ከመፍጠር ባሻገር፣ የዚህ እንቅስቃሴ አንዱ እና ዋነኛው ስኬት አንባቢውን ስለጥቁር ህይወት ያላቸውን ትኩረት ወደ የነጭ እና የጥቁሮች የፍቅር ታሪክ እንዲሰረቅ ማድረጉ ነበር። እንደ ሶኒያ ሳንቼዝ፣ ኒኪ ጆቫኒ፣ ኢንትዛኪሻንጌይ፣ እና ሌሎች በርካታ የንቅናቄው ቀራጺዎች ልዩ የሆነወን የጥቁር ሴቶች ተመክሮ ዋና የታሪካቸው መነሻ አድርገው ፅፈውበታል። በጥቁሮች ህይወት ውስት የጾታ እና የዘር ግንኙነቶችን በማሳየት የጥቁሮችን ውስጣዊ ህይወት እና የማህበራዊ አለምን ከነጮች ጋር ባልተዛመደ መልኩ የማቅረብ መንገድን ከፍትዋል። ባልድዊን በራሱ ስራ ላይ የዘርን የሁለትዮሽ ቦታ በመቀየር እንዴት በጥቁር መቀራረብ እና ውስጣዊነት ላይ ማተኮር እንደሚቻል በ If Beale Street Could Talk/የቢል ስትሪት ማውራት ቢችል እና እሱን ተከትለው በወጡት መጽሃፎች ለአንባቢዎቹ ማሳየተን ችልዋል። If Beale Street Could Talk/የቢል ስትሪት ማውራት ቢችል ተመሰርቶ በተሰራው ፊልም ላይ ባሪ ጄንኪንስ ስራውን በሚማርክ እና በሰላማዊ መግለጫ አስደግፎ እንዲሁም ለቲሽ የተራኪነትን ቦታ በመስጠት የመጀመሪያ የሰው ተአማኒነትን እንዲጎናጸፍ በማድረግ ወደ ትልቅቁ ስክሪን ባስደናቂ መንገድ ቀይሮታል። ከዚህም ባሻገር ጄንኪንስ ስለ ባልድዊን ስራ በተመልካቾች ከሲቪል መብቶች ጋር ብቻ ተያይዞ በስፊው የመጠራቱን ሁኔታ ሊቀየር የሚችል ስራ አስተዋውቆናል። ዳይሬክተሩ ባልድዊን በአምባቢዎች እምብዛም የማያጋጥም አዲስ የፍቅር መብት ብሎም ተመልካቾች በፊልም ቲያትር ቤቶች ውስጥ እምብዛም የማይታይን የጥቁር ራእይ የሚገልፅ ስራ ሰርትዋል።
ባልድዊን በህይወቱ በስተመጨረሻ ባሳተመው To Crush a Serpent /እባብን ሸረኛን መጨፍለቅ የተወሳሰብን መሆናችን ብቸኛው ደህነነታችን ነው። “የመብሰላችን ዋነኛው ቁልፍም ፊቅር ብቻ ነው።” ሲል ጽፍዋል። በብዙ መልኩ በስሜት ያለመብሰል ብሎም ቀላል አስተሳሰብ እንደ ጥንካሬ በሚታይባት ሃገር ውስጥ፣ የባልድዊን የጎለበተ አስተሳሰብ በዋጋ ሊተመን የማይችል ሃብት በመሆኑ ለአሜሪካ የጋራ ደህንነት የሚረዳ ንድፍ ሊሆን ይችላል።
ዳግማዊ ውብሸት የአሀጁ ቤተሰብ በፔንሲልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንታዊ ስብስብ የኢንግሊዘኛ ፕሮፌሰር ሲሆን The Calendar of Loss: Race, Sexuality, and Mourning in the Early Era of AIDS/የጥፋት ወቀት፣ ዘር፣ ጾታዊነት እን ሃዘን በመጀመሪያው የኤድስ ጊዜያት የሚለወን መጽሃፍ ጸሃፊ ነው።
ጽሁፍ: ፕሮፌሰር ዳግማዊ ዉበሸት
ትርጉም: መና