ይህ እ.ኤ.አ በጥር ወር 2019 ላይ አትላንቲክ ለተሰኘው ታዋቂ መጽሔት በዶክተር ዳግማዊ ዉበሸት የተጻፈ ጽሑፍ ሲሆን የጄምስ ባልድዊን የፍቅር ጽሑፎች በጊዜ ሂደት እንዴት እንዳደጉ እና እንደተሻሻሉ ያሳየናል። ጄምስ ባልድዊን በሰዎች መካከል የሚፈጠሩ ጥልቅ እና ስሜታዊ የሆኑ ግንኙነቶች በአሜሪካ ውስጥ ተስፋፍቶ የሚታየውን የዘር መከፋፈል እና መድሎ ይፈውሳል የሚለውን አንኳር አስተሳሰብ እንደሚያራምድ የታወቀ ነው።
በጊዜዉ ከጻፋቸው በርካታ ጽሑፎች ዉሰጥ እ.ኤ.አ በ 2019 በተለያዩ የፊልም ሽልማቶች ላይ ነግሶ በታየው በባሪ ጄንኪንስ የተሰራው ‘If beale street can talk’ የተሰኘዉ ፊልምን መጥቀስ ይቻላል። ይህ ፊልም ጄምስ ባልድዊን ሁለት ጥቁር ወጣት ፍቅረኞች በነጮች የበላይነት በምትመራው አሜሪካ ውስጥ እንዴት እንደሚፈተኑ በሚይሳየው ግሩም ልቦለድ ላየ ተመስርቶ የተሰራ ነው። ይህ ፊልም በጊዜው የነበረውን የጸሃፊውን ስራ በደንብ እንድንረዳ ከማድረጉም በላይ የጸሓፊው ስራዎች ከቀድሞው ባላነሰ ሁኔታ ዛሬ ላይ ሆነንም አስፈላጊ እና ጠቃሚ መሆናቸውን ያሳየናል። የባልድዊን የጽሑፍ የጊዜ ዑደት ከ1947 – 1987 ባለው አራት ዓሥርት ዓመታት ውስጥ የቆየ ሲሆን፤ በነዚህ አመታት ውስጥ አሜሪካ ግዙፍ ሊባሉ የሚችሉ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ለውጦችን አስተናግዳለች። በነዚህ ጊዚያቶች የጸሓፊው የሥነ ጥበብ ራዕይ አብሮ እያደገ እና እየጎመራ ሄዷል።
እ.ኤ.አ በ1974 የታተመው ‘If beale street can talk’ ሁለት ጥቁር ፍቅረኞች እንዴት በሃሰት ወንጀል ምክንያት ህይወታችው እንደሚመሰቃቀል እየተነተነ ግሩም በሆነ አተራረክ ያስቃኘናል። ይህ ጽሑፍ ባልድዊን ወደ መጨረሻው የስራ ጊዜዎቹ የተከተላቸዉን የአጻጻፈ ስልት በጉልህ ሁኔታ ከማሳየቱም በላይ፤ ባልድዊን ለስራው ፍቅር የሚባለውን ጽንሰ ሃሳብ ከምንም በላይ ገዢ የሆነ ጭብጥ አድርጎ እንደሚጠቀመው ማሳያ ነው።ኘ ‘If beale street can talk’ በተለያየዩ የፊልም ሃያስያን ህትመቶች የተለያዩ እና የተደበላለቁ ግምገማዎችን አግኝቷዋል። አንዳንዶች በውስጡ በሚገኘው ግሩም እና ስስ የፍቅር ታሪክ አድናቆታቸውን ሲቸሩት ሌሎች ደግሞ ስለ ተራኪው ድምጽ ትክክለኛ አለመሆን ነቅፈውታል። አሁን ላይ ሆነን እንደ ታዳሚ ይህንን የባልድዊንን ስራ ወደሁዋላ ስንመለከተው አንድ ነገር ግልጽ ሆኖ ይታየናል። ይህም እንዴተ ባልድዊን ስለ ፍቅር ያለውን ራእይ እና እንዴት በወቅቱ በጥቁር አሜሪካዊያን ቤተሰቦች መሃከል ያለውን የእርስ በእርስ ጠንካራ ስሜት የሁለት ወጣት ጥቁር ፍቅረኞችን ታሪክ በመጠቀም መግለፁን ያሳየናል። ባልድዊን ከዚህ ጽሑፉ በፊት ያለፉትን አስርት አመታት ስለ ፍቅር በመጻፍ እና በማሰብ ያሳለፈ ከመሆኑም በላይ እንደ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ልምዱን ሲጽፍ ከመቆየቱም በላይ ፍቅር በሃገሪቱ ተስፋፍቶ የሚገኘውን የዘር ክፍፍል ሊሰብር አንደሚችል በጽሑፎቹ ሲሰብክ ቆይትዋል።
በብዙ አሜሪካውያኖች ጭንቅላት ውሰጥ 1960ዎቹ የስነጽሑፍ ጊዜያት ለባልድዊን የተሰጠ አድርገው ይወስዱታል። ይህም በዚያ ወቅት ከባልድዊን ዉጪ ግዜዉን ተቆጣጥሮ የቆየ ጸሃፊ አለመኖሩን ያሳየናል። ምንም እንኳን ባልድዊን በ1950ዎቹ ተደናቂነትን ያገኘባቸውን ስራዎች ቢያሳትምም ‘Another Country’ (1962) እና ሁለት ድርሰቶች አንደአንደ የወጡበት ‘The Fire Next Time’ (1963)፣ የተሰኙት ስራዎቹ ጸሃፊውን ተቀዳሚ እና ተጠሪ ምሁር አድርገውታል። በዚህ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች እና ስራዎች በሰፊው በተስፋፋበት ወቅት ጸሃፊው የነጭነትን ሃይል በመመርመር እና ስለፍቅር በመስበክ የአሜሪካን የወደፊት ተስፋ እና አቅም ለማሳየት ችሏል።
በ1960ዎቹ ከወጡት የባልድዊን ጽሑፎች ‘Another Country’ የጸሃፊውን ስራ በዋናነት ይወክላል። ይህ ጽሑፍ የነጭ የበላይነት ላይ ጠንካራ እና ተጨባጭ ተቃውሞን ይዞ ከመቅረቡም በላይ እንዴት የነጭ የበላይነት የጥቁር ሰዎችን መገዛት አንደሚያስፋፋ ያሳየናል። ከዚህም ባሻገር ያልተመጣጠነ የሃይል የበላይነት እንዴት በአሜሪካ በሰዎች፣ በተቋሞች፣ እና የሰፊውን የሃገሪትዋን የሞራል ባህሪ ይዞ እንደሚገኝ በሰፊው የገለጸ ስራ ነው። በዚህ ጽሑፉ ባልድዊን እንዴት እራስን “ከተጠያቂነት ነጻ ማድረግ” የነጭ የበላይነት ዋና መለያው እንደሆነ በጠንካራ ሥነ ጽሑፍ ያብራራልናል። በራሱ ቃላቶች አንደሚገልጸው፥ “ብዙ ውድመትን ያደረሰ ወይም ያቀናበረ ክፍል ንጹህ መሆን አይፈቀድለትም። ይህ ንጽህና ነው ወንጀሉን የመሰረተው።” በዚህ ንግግሩ ውድመትን በማድረስ ሲል ባርነትን፣ ማቁሰልን፣ ብሎም የሰዎችን መብት በሃይል መንፈግን ይጨምራል። ይህንንም ለመቀየር የተለያዩ ተቃውሞዎች እና እንቅስቃሴዎች እንደሚያስፈልጉ ይሰብካል። ትክክለኛነት እና ንፅህናን ባልድዊን የአሜሪካ ሃይለኛ የዘረኝነት ታሪክ እንደ ጭምብል ከመሸፈኑም በላይ የነጭ አሜሪካዊያንን የሦስተኛ ወገን ሃላፊነት እንዳያገናዘቡ ያረጋል። ይህ አመለካከት ስለ ሃገራቸው ብሎም ስለራሳቸው ያላቸውን አስተሳሰብ የከበረ በማድረግ የሃገሪትዋን እውነተኛ ታሪክ ድብቅ እንዲሆን ያረገዋል። ባልድዊን ንጽህና የሚለው ነጭ አሜሪካዊያን ከመሆን ጋር የሚመጣ መሆኑን ከመግለፁም በላየ ይህ ሃሳብ ካልጠፋ በሃገሪቱ ዘርን በተመለከተ ያለውን ተጨባጭ ችግር እንደማይቀየር ያምናል።
ባልድዊን ስለፍቅር ሃሳቡን አስረግጦ ለምግለጽ ፍቅርን አሸናፊ፣ አነጋጋሪ ብሎም የተለየ ስሜትን የሚፈጥር በማድረግ ስራዎቹ ላይ ያቀርበዋል። እንደውም ከነጭነት ጋረ በተያያዘ የሚመጣውን የንጹህነት ብሎም እራስን ከተጠያቂነት የማውጣት ሃሳብን ይፈውሳል ብሎ እንደብቸኛ መፍትሔ ያቀረበው ፍቅር እና ፍቅር ብቻ ነበር።
“ፍቅር በሩን ካላወዛወዘ ሌላ ሃይል አያደርገውም ወይም አይችልም።” በሚለው ንግግሩም ይታወቃል።
ጽሁፍ: ዶክተር ዳግማዊ ዉብሸት
ትርጉም: መና