Categories
Uncategorized

የመለወጥ እርዳታ

የመለወጥ እርዳታ የተለያዩ መንገዶችን ማለትም ህክምናን ጨምሮ የእምነት እና ባህላዊ ስርአቶችን እና ብጀቶችን በመጠቀም የአንድን ሰው ጾታዊ ማንነት ለመቀየር ወይም የጾታዊ ስሜትን ለመቀነስ የሚደረግ እርዳታ ነው። የመለወጥ እርዳታ ክዊር መሆንን እንደበሽታ፣ ሱስ ወይም የሰይጣን ዉጤት ነው የሚለወነ ጽንሰ ሃሳብ የሚያፀድቅ ነው። ምንም እንኩዋን የመለወጥ እርዳታ በተለያዩ የሳይንሳዊ ጥናቶች መሰረት የሌለወ፣ ጥናታዊነትን ያላማከለ ብሎም ጎጂ ተበሎ ቢፈረጅም በተለያዩ የአለም ክፍሎች በሰፊው እየተካሄደ ይታያል። የስነልቦና ጥበብን በመጠቀም የሚደረገው የመለወጥ እርዳታ ባደጉት ሃገራተ የተለመደ ሲሆን በሃገራችን በእምነት ተቖማት፣ በተለያዩ የባህላዊ እምነቶች ለምሳሌ ጥንቆላ/ዉቃቤ እና በባህላዊ ህክምና ተቖማት ውስጥ በሰፊው ሲካሄድ ይታያል። ምንም እንኩዋን ባሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የአለማችን ክፍሎች በብዛት እየተካሄደ ባይታይም የቀዶ ህክምናን፣ ሾክ ቴራፒን፣ እና ወሲባዊ በደልን በመጠቀም የሚደረግ የመለወጥ እርዳታ እ.ኤ.አ 1940 – 1980ዎቹ በአለማችን ተስፋፍቶ ይካሄድ ነበር።

በሃገራችን በቀዳሚነት አሉ በሚባሉት የእምነት ተቖማት፣ ባህላዊ እምነቶች አና ባህላዊ የህክምና አዋቂዎች የመለወጥ እርዳታን እስካሁን ድረስ በሰፊው ሲሰጡ ይታያል። በኢትዮጲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነተ ተከታዮች ዘንድ የመለወጥ እርዳታ የአንድን ሰው የጾታ ማንነት ከመቀየሩም በላይ ከሰይጣን ወይም ከባእድ ሃይል መንፈስ ከሚመራ የህይወት መንገድ ያድናል ተብሎ ይታመናል። የኢትዮጲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነተ ተቖማት የመለወጥ እርዳታን በሰፊው ከመስጠታችውም በላይ የሌላ የእምነት ተቖማቶችን በማነሳሳት እና በአንደ ጥላ ስር በማድረግ ስለኢትዮጵያ ዝም አንልም፥ ትውልድን ከግብረ፡ሰዶም እንታደግ የሚለ ማኅበር መስረትዋለ። ይህ ማሀበር እ.ኤ.አ በህዳር 2019 ህጋዊ ሂደቱን በጠበቀ ሁኔታ የተመዘገበ ሲሆን ዋናው አላማው መንግስት በተመሳሳየ ጾታ አፍቃሪዎች ላየ ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድ ብሎም በቤተክርስትያናት የሚመራ የመለወጥ እርዳታ እንዲስፋፋ ነው። የመለወጥ እርዳታ በኢቲዬጲያ በሰፊወ ተቀባይነት ባላችው የሙስሊም እና የኦርቶዶክስ የእምነት ተከታዮች በስፊወ ተአማኝነት አለው።

በኦርቶዶክስ የእምነት ተከታዮች ዘንድ የመለወጥ እርዳታ የእምነቱ መሪዎች በሚባሉት ቄሶች በሚመራ የፆም፣ ጸሎት፣ ምልጃ እና የጸበል መጠመቅ ስነስረአት ከሰባት ቀን እስከ ሰደስት ወረ በሚፈጀ ሁኔታ የአንድን ሰው የጾታ ማንነት ለመቀየር ሙከራው የካሄዳል። በተመሳሳየ ሁኔታ በሙስሊም የእምነቱ ተከታዮች የመለወጥ እርዳታ በቁርአን አዋቂዎች ወይም በሼኮች እና የሀይማኖት አባትች በመመራተ በሰፊው ሲካሄድ ይታያል።

ብዙ ክዊር ኢቲዬጲያኖች በተለያዩ አጋጣሚዎች ወይም በጟደኛ እና በቤተሰብ ግፊት በተለያዩ እምነቶች ዉሰጥ ሆነው የቤተከክርስቲያንን አና የመስኪዶችን ደጃፍፎች በማዘወተር እራሳችዉን ለመቀየር እንደሚሞከክሩ ይሰማል።

በቅርብ ጊዜ አንዱ ወዳጃችን እራሱን ለመቀየር ከሞከረበት መንገድ ጸበለ ዋነኛው መሆኑነ አጫዉቶናል። በዚህም ሂደት ወስጥ ሆኖ ጸበለ ለመጠመቅ በሄደ ቁጥር አራቁታችውን ሆነው አንደሱ ለመፈወሰ የሚመጡት ወንዶችን ሲያያችው የባሰ ጌይነቱንሰለጨመረበት ጸበልን እርም ብሎ አንደተወ ልምዱን አጋርቶናል። በጸበል ለመፈወስ በሚደረገው ሂደት ዉሰጥ ወንዶች እና ሴቶች ተለያይተው አንደሚጠመቁ አንባቢው ልብ ይለዋል።

ሌላዋ ወዳጃችን በተመሳሳይ ሁኔታ የጾታ ማንነትዋን ለመቀየር ጸበል በሄደችበት ጊዜ የቄሱ አስተያየት እንዳላማራት ብሎም በመስቀል ስትደበደብ ህመሙ እጅግ እያስደሰታት ሰለመጣ ሌላ ሃጢያት አልጨምርም በማለት አንደቀረች ያጫወትችንን አንደአዝናኝ አጋጣሚ ሳልጠቅሰው አላልፉም። የመለወጥ እርዳታ በሃገራችን ከእምነት ተቖማት ባለፈ ሁኔታ በተለያዩ የባህላዊ እምነቶች ለምሳሌ ጠንቐይ ቤት በመሄድ ወይም በባህላዊ ሀክምና ሰጪዎች በሰፊው ይሰጣል።

የሰውን የጾታ ማንነት ለመቀየር የሚደርጉ ህክምናዋች ከ1970ዋቹ ጀመሮ በበዙ የአለማችን ክፈሎች በሚሰጡ የህክምና አገልገሎቶች ውሰጥ መሰጠት እንደቆመ ብዙ ጥናቶች ያሳያሉ። ይህም ብዙ የህክምና ተቐማት የተመሳሳይ ጾታ ማንነት ተፈጥሮአዊ ነው የሚሉ የተለያዩ ጥናቶች መውጣታቸዉን ተከተሎ ነው። እንዲሁም እ.ኤ.አ በ1990 የአለም የጤና ተቐም (WHO) ክዊር መሆንን ከበሽታ ብሎም ከስነ አእምሮ ችግር ጋር የተያያዘ አለመሆኑነ ማረጋገጣችውን ተከትሎ ብዙ ያለማችን ክፋሎች የመለወጥ እርዳታን እንደ ጎጂ ልማደ ፈርጀዉታል። ምንም እንኯን በርከት ያሉ ያለማችን ሃገሮች የመለወጥ እርዳታን በህግ ቢያስቐሙትም ሀገራችንን ጨምሮ በተለያዩ በማደግ ላይ ባሉ እና ባደጉ ሃገራት ላይ ህጋዊ ሆኖ ቀጥልዋል። እ.ኤ.አ በግንቦት ወር 2020 በዩኤንኤችሲአር (UNHCR) ስር በወጣው ጥናት ላይ የመለወጥ እርዳታ ሰዎች እራሳችውን እንዳይቀበሉ በማድረግ ለሚመጣ የራሰ ማጥፋት ሙከራ ሃያ ሰባት በመቶወን እንደሚይዝ አረጋግጠዋል።

ምንም እንኯን የተለያዩ ጥናቶች የመለወጥ እርዳታን ጎጂ የህክምና እና ባህላዊ ልመድ ብለወ ቢፈርጁትም፣ አስከዛሬ ድረሰ በተለያዩ ሃገሮች ዉስጥ ህጋዊ ሆኖ ይታያል።

የመጀመሪያ የአእምሮ ጤና እርዳታ አሰጣጥ የኢቲዬጲያ ልምድ፣ እድል እና ፈታኝ ሁነቶች በምሰራቅ አፍሪካ ሃገሮች በሚል ርእስ እ.ኤ.አ በ2016 በአማኑኤል ሆስፒታል ስር በወጣው ጥናት ላየ ከሃያአምስት ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ ኢትዬጲያን የአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ አንደሚጠቁ ከመጥቀሱም በላይ የሚሰጠዉ አገልግሎት ተደራሽነት እጅግ አናሳ እንደሆነ የጠቀሳል። ጥናቱ የሃገሪትዋን የስነአእምሮ እርዳታ አሰጣጥ የተማሩ ባለሙያዎች ተመጣጣኝ ያልሆነ እጥረት የሚታይበት እንደሆነ ብሎም ከሌሎች የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች አንጻር ምልከታ የጎደለው መሆኑን ያረጋግጣል።

የመለወጥ እርዳታ የሚለወን ርእሰ ይዘን ሁለት የአእምሮ ህክምና ባለሙያዎች ሰለመለወጥ እርዳታ እና በሀገራችን ሰላለው ሁኔታ እንዲያሰረዱን በጠየቅናቸው ጊዜ በአበዛኛው የሚሰጡ የአእምሮ እርዳታ አገልግሎቶች ስር የሰደደ የተደራሽነት ችግር ስላላችው ከጾታዊ ማነነት ጋረ በተያያዘ የሚመጡ ጥያቄዎችን እንደህክምና አገልግሎት ተቖም የአእምሮ ጫና ፈጣሪ ብሎ እንደማይቆጠር ነግረዉናል። ያማከርናቸው የስነልቦና ባለማያዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ከጾታዊ ማነነት ጋረ በተያያዘ የመለወጥ እርዳታን እንደዋነኛ የማከሚያ መንገድ ሆኖ ሲመረጥ ማየታቸውንም ነገረዉናል። የህክምና ባለሞያዎች ከጾታዊ ማንነት ጋር የሚገጥሙዋቸውን ጉዳዮች ለጉዳዩ ባላቸው የግል አቁዋም እና በጉዳዩ ላየ ባላቸው የግል እውቀት በመመስረት የራሳቸውን የህክምና አስጣጥ ምርጫ ይወስዳሉ። ከዚህ በዘለለ ስለ መለወጥ እርዳታ በሃገራችን ህክምና አገልግሎቶች ስር ያለውን አቋም እና አሰራር ላይ ለማገኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርትዋል። ወደፊት የመለወጥ እርዳታ አና የሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ይዘንላችሁ አንደምንመጣ እንገባለን።

የዚህ ወር የአርትኦት ጽሁፋችንን ስንደመድምም የክዊር ማህበረሰባችን ስለ መለወጥ እርዳታ ምን ያህል ያውቃል? እራሳችንን ለመቀየር ያረግናችው ሙከራዎች እንዴት ነበር? ምንስ ተማርንባችው? የሚሉትን ጥያቄዎች እንድነወያይበት በማቅረብ ይሆናል።

መልካም ወር።

ጽሁፉ: ሌይቲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *