Categories
Uncategorized

ከትላንት

ከትላንት በሚለው አምዳችን በተለያዩ የዐለም ክፍል ውስጥ የተከሰቱ ሁነቶችን፣ የስነጥብ ስራዎችን አንዲሁም የሰባዊ መብት የማስጠበቅ እንቅስቃሴዋችን እናቀርባለን። በዚህ የመጀመሪያው ምእራፉችን ታውቂው የኢሴንስ መጽሄት እንደ . . . አቆጣጠር 01/06/2021 ያወጣቸውን የአመቱን አስራ ስድስት መታወቅ የሚገባቸውን ጥቁር ክዊር አርቲስቶች አቅርበንላችዃል። 

ክዊር አርቲስቶች የኪነጥበብ መሃበረሰብ የልብ ትርታ ናቸው። ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ፣

የተመሳሳየ ፆታ ወንዶች እና ሴቶች ብሎም በሁለቱም ጾታዎች የማይወከሉ አርቲስቶች በተለያዩ የስነጥበብ መድረኮች ላይ የማይወደዱ ስሜቶች እና አገላለጾችን ይዘው ቆይተዋል። ሰአሊዎች፣ የምስለ ቀረጻ ባለሙያዎች፣ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች፣ ኮላዥ ሰሪዎች(የተለያዩ ምስሎችን በማቀናጀት የሚሰራ ጥበብ) እና በተለያዩ ስራዎቻቸው እራሳችንን አልፎም ሌሎችንም ለመረዳት አስችለወናል ።

እነዚህ የፈጠራ ስራዎች አመቱን ሙሉ ትኩረት እና ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል። ይህንን ስራ እንደ ብላክ ትራንስ ፌምስ ኢን ዘ አርትስ ( Black Trans Femmes in the Art) ፣ አይኤስኢ – ዲኤ (ISE-DA) እና ዘ ክዊር ቢኔአል (Queer Biennial) ያሉ ድርጅቶች በሰፊው የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር እየሰሩ ይገኛሉ።

ዛሬ የኩራት ወርን (pride month) የመጀመሪያ ቀን እንደመሁኑ እነዚህን ጥቁር የዘመናችን አርቲስቶችን እንዲሁም ስራቸው የፈጠረውን የክዊር ታይነት በመጨመር ብሎም የጾታ ግንዛቤን በመፍጠር ያሳለፉትን ተጽእኖ በማክበር ይሆናል። እነዚህ ሊታወቁ የሚገቡ አስራ ስድስት የክዊር (LGBTQ) የምስላዊ አርቲስቶች ናቸው።


Julie Mehretu

ጁሊ ምህረቱ የምህረቱ እጅግ ማራኪ እና ትንፍሽ አስቆራጭ የሆኑ የስዕል ስራዎች በ ዊትኒይ እና ጀሚኒ (Whitney and Gemini G.E.L) ዓውደርኢ ላይ ቀርበዋል።

Shantell Martin

ሻንቴል ማርቲን ስዕል መሳል የጀመረችው በአከባቢዋ ካለው የክዊር ማንነት ጥላቻ ለማምለጥ እንደሆነ ለኢሴንስ (ESSENCE) ገልጻለች።

Kehinde Wiley

ኬሂንዴ ዊሌይ በ2015 በብሮክሊን ሙዚየም (Brooklyn Museum) ካቀረበው እጅግ አስደማሚው ትርኢቱ ሳናገግም ፣ ዊሌይ በ 2018 የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ገላጭ ምስልን የሳለ የመጀመሪያው ግልፅ የወጣ ወንድ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ግለሰብ ለመሆን ችለሏል ።

Danielle Scott

ዳንኤል ስኮትስኮት የድብልቅ ጥበብ ባለሞያ ስትሆን በ አክዋባ አርት ጋለሪ (Akwaaba Art Gallery) እና በ ኢንዴክስ አርት ጋለሪ (Index Art Gallery) ለብቻዋ ስራዎቿን አቅርባለች ። በተጨማሪም በ ሲቲይ ዊዝ አውት ዎልስ (City Without Walls) እና በ ዘ ፓውል ሮብሰን ጋለሪ (The Paul Robeson Gallery) በተካሄደ ዓውደርኢ ላይ ስራዎቿን ከሌሎች የጥበብ ሰዎች ጋር ህብረት አቅርባለች ።

Kendrick Daye

ኬንድሪክ ዳዬ የድብልቅ ጥበብ ባለሙያ የሆነው ዳዬ አላማው ምናባዊ የሆነ የወደፊቱን እየበለፀገ እና እየተመነጠቀ የሚሄድን ክዊር ሰዎችን የሚገልፅ ስራዎችን መፍጠር ነው ። በቅርቡ የጥቁር ክዊር ጥንቆላ (The Black Queer Tarot) የሚል ዘመቻ አስጀምሯል ።

Leilah Babirye

ለኢላህ ባቢርዬ ኡጋንዳ የተወለዱት ባቢርዬ ሁለገብ የጥበብ ባለሙያ ሲሆኑ በዕለትተለት የምንጠቀማቸውን እቃዎች ወደ ጥበብ ስራዎች በመቀየር ማንነትን ፣ ተማርኮን እና የሰብአዊ መብትን ይዳስሳሉ ።

Mickalene Thomas

ሚካሌኔ ቶማስ በቶክዮ ፣ በብሮክሊን ፣ በሎስ አንጀለስ እና በኒው ኦርሊየንስ ዓውደርኢ አቅርባ ታውቃለች ፤ ነገር ግን እኛ በፍቅር የወደቅነው በ ዌስት ፓልም ቢችስ ኖርቶን የጥበብ ሙዚየም (West Palm Beach’s Norton Museum of Art) በቀረበው የናኦሚ ካምቤል ገላጭ ምስል ነው ።

Jonathan Lyndon Chase

ጆናታን ላይዶን ቼስ መሰረታቸውን በፊላዴልፊያ ያደረጉ የጥበብ ባለሙያ ሲሆኑ በኒው ዮርክ እና በቻይና የነጠላ ዓውደርኢ አቅርበዋል ።

Zanele Muholi

ዛኔሌ ሙሆሊ ደቡብ አፍሪካዊ የጥበብ ሰው ሲሆኑ በለንደን ታሌስ ሙዚየም (London’s Tate Museum) ለብቻቸው ባቀረቡት አውደርኢ የምስሎችን ግንዛቤን የማስቀየር አቅም አሳይተዋል።

Isaac Julien

አይዛክ ጁሊየን የተንቀሳቃሽ ምስል ባለሙያ ሲሆን የ1989ኙ ሉኪንግ ፎር ላንግተን (1989’s Looking for Langston) ላይ አሻራውን አሳርፏል ። በኒው ዮርክ ሰለሞን አር. ጉግኔም ሙዝየም (New York’s Solomon R. Guggenheim Museum) ፣ በፓሪስ ሴንተር ፖምፒዶ (Paris’ Centre Pompidou) እና በኬፕ ታውን ዜኢትዝ ዘመናዊ መዝየም (Cape Town’s Zeitz Museum of Contemporary Art) ውስጥ ስብስቦቹ ተካተው ይገኛሉ።

Lyle Ashton Harris

ለይል አሽተን ሐሪስ የአሽተን ሐሪስ የጥበብ ስራዎች ምስልን ማስቀረት ፣ የክዋኔ ጥበብ እና የተለያዩ ወረቀቶችን እና ምስሎችን በመቁረጥ እና በማጣበቅ አንድ ወጥ የጥበብ ስራን መፍጠርን በጥምረት የያዘ ነው ። እንደ ጆን ሲሞን ጉጌንኀም ሜሞሪያል ፋውንዴሽን (John Simon Guggenheim Memorial Foundation) እና ዘ ሃይ ሙዚየም ኦፍ አርት (The High Museum of Art) ከመሳሰሉ ብዛት ካለቸው የተከበሩ ተቋማት የተለያዩ የትምህርት እድሎችን እና ሽልማቶችን አግኝተዋል ።

Paul Mpagi Sepuya

ፖል ኤፓጊ ሴፑያሴፑያ ምስልን የማስቀረት ባለሙያ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በሃርለም ስቱዲዮ ሙዚየም ( Harlem Studio Museum ) ውስጥ በመግባት የጥበብ ስራ ሙያን ቀስመዋል ።

Sable Elyse Smith

ሳቤል አለይስ ስሚዝ አለይስ ስሚዝ ምስልን ፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ፣ ፊደላትን እና ሌሎች የጥበብ መንገዶችን በማቀናጀት የጥበብ ስራዎችን የምትፈጥር ሁለገብ የጥበብ ሰው ነች ። በስራዎቿ ከክርኤቲቭ ካፒታል (Creative capital) ፣ ከፋይን አርትስ ዎርክ ሴንተር (Fine Arts Work Center) ፣ ዘ ክዊንስ ሙዚየም (The Queens Museum) ፣ ከስካውሊገን የስዕል እና የቅርጻቅርጽ ትምህርት ቤት (Skowhegan School of Painting and Sculpture) ፣ ከሬማ ሆርት ማን ፋውንዴሽን (Rema Hort Mann Foundation) ፣ ከ ዘ ፍራንክሊን ፉርናስ ፈንድ (The Franklin Furnace Fund) ፣ ከ አርት ማተርስ (Art Matters) እና ከሌሎች ትልልቅ የጥበብ ተቋማት እውቅናን አግኝታለች ።

Juliana Huxtable

ጁሊያን ኅክሥብል ኅክሥብል መቀመጫዋን በኒው ዮርክ ያደረገች የምስላዊ ጥበብን ከሙዚቃ አጫዋችነት ጋር አጣምራ የምትከውን ባለሙያ ነች ። ስራዎቻቸውን በሞማ ፒኤስ1 (MoMA PS1) ፣ ዊትኒይ ሙዝየም ኦፍ አሜሪካን አርት (Whitney Museum of American Art) እና በ ዘ ኒው ሙዚየም ኦፍ ኮንቴምፖራሪ አርት (The New Museum of Contemporary Art) ዓውደርኢዎች ላይ አቅርበዋል።

Naima Green

ኒኣማ ግሪን ግሪን ለ ሃርፔር ባዛር ሽፋን የሶላንጅን ምስል ካነሳች በኋላ በተመሳሳይ ዓመት በፎቶግራፊስካ ኒው ዮርክ (Fotografiska New York) ዓውደርኢ ላይ ፔርሱት ሶውት ቱ ፕሬቨንት LGBTQ ኢሬሰር (Pur·suit sought to prevent LGBTQ erasure) በሚል ርዕስ የLGBTQ ማህበረሰብ መገፋት ላይ የሚያጠነጥነው ስራዋ ሽፋን አግኝቷል ።

Texas Isaiah

ቴክሰስ አይዜያ አይዜያ ዓውደርኢያቸውን በሃርለም ስቱዲዮ ሙዚየም (Studio Museum in Harlem) እና በሎስ አንጀለስ ሃመር መዚየም (Los Angeles’ Hammer Museum) አቅርበዋል ። የኛ ጨረቃ (Our moonlight) በሚል የወጠኑት ስራቸው Covid-19 አስጨናቂ በነበረት ወቅት የምንፈልገውን መቀራረብ አስቃኝቶናል።


ኢሴንስ ማጋዚን, 06/2021

ትርጉም፥ ኦርዲነሪ ዛክ