አርትኦት

የመለወጥ እርዳታ

የመለወጥ እርዳታ የተለያዩ መንገዶችን ማለትም ህክምናን ጨምሮ የእምነት እና ባህላዊ ስርአቶችን እና ብጀቶችን በመጠቀም የአንድን ሰው ጾታዊ ማንነት ለመቀየር ወይም የጾታዊ ስሜትን ለመቀነስ የሚደረግ እርዳታ ነው።  የመለወጥ እርዳታ ክዊር መሆንን እንደበሽታ፣ ሱስ ወይም የሰይጣን ዉጤት ነው የሚለወነ ጽንሰ ሃሳብ የሚያፀድቅ ነው። ምንም እንኩዋን የመለወጥ እርዳታ በተለያዩ የሳይንሳዊ ጥናቶች መሰረት የሌለወ፣ ጥናታዊነትን ያላማከለ ብሎም ጎጂ ተበሎ ቢፈረጅም በተለያዩ የአለም ክፍሎች በሰፊው እየተካሄደ ይታያል። የስነልቦና ጥበብን በመጠቀም የሚደረገው የመለወጥ እርዳታ ባደጉት ሃገራተ የተለመደ ሲሆን በሃገራችን በእምነት ተቖማት፣ በተለያዩ የባህላዊ እምነቶች ለምሳሌ ጥንቆላ/ዉቃቤ እና በባህላዊ ህክምና ተቖማት ውስጥ በሰፊው ሲካሄድ ይታያል። ምንም እንኩዋን ባሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የአለማችን ክፍሎች በብዛት እየተካሄደ ባይታይም የቀዶ ህክምናን፣ ሾክ ቴራፒን፣ እና ወሲባዊ በደልን በመጠቀም የሚደረግ የመለወጥ እርዳታ እ.ኤ.አ 1940 – 1980ዎቹ በአለማችን ተስፋፍቶ ይካሄድ ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ

ስም አልባ የክዊር ኢትዮጲያዊያንን ታሪክ ፣ ባህል ፣ ማንነት እና የቀን ከቀን ህይወትን የሚዳስስ ሀገር በቀል ማህበር ነው ። 

ክዊር ለሚለው ቃል ቀጥተኛ እና ገላጭ የሆነ የአማርኛ ትርጉም  በማጣችን እ. ኢ. አ. በ1993 የወንድ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች የተለያየ የመገናኛ ዘዴዎችን ለመፍጠር ብለው በመሰረቱት ያሆ ግሩፕ ( yahoo group ) ላይ በፈጠሩት የመገናኛ ገፅ ማንነታችንን ይገልጻል ብለው በማሰብ ዜጋ የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ