ስለ ስም አልባ

ስም አልባን ተደብቆ የቆየውን የክዊር የማህበረሰባችንን ታሪክ ፣ ማንነት እና ህልውና በግልፅ በማቅረብ እኛ ጋር ያለውን እውነታ ለሃገራችን ብሎም ለተቀረው የዓለም ክፍል ለማሳወቅ ተነስትዋል።

ራእይ

የስም አልባ ራእይ ፈጠራና ጥበብ በተሞላ አገላለጽ አማካይነት ስለ ድብቁ የክዊር ማኅበረሰብ ለኢትዮጵያውያን እና ለዓለም ግንዛቤን በማሳደግ ጠንካራና የተባበረ የክዊር ማኅበረሰብ መፍጠር ነው፡፡

ተልእኮ

ስም አልባ በፆታዊ ተማርኮ ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸመውን መድልዎ እንደ መቀነሻ መንገድ የሚድያ ዘርፎችን ትክክለኛ፣ ተገቢና አካታች እንዲሆኑ በማረጋገጥና በማሳደግ ዙሪያ ላይ ይሰራል፡፡